Wednesday, May 9, 2012

አስኳሉ የተሐድሶ ሕዋስ ማኀበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡



እንቅስቃሴውን አቡነ ጳውሎስ፣ አቡነ ገሪማ፣ አባ ሰረቀ ብርሃን፣ በቅርቡ ከአሜሪካ ተመለሰው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ///ያንና ጉዳይ ፈፃሚ የሆነው ኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን እና ሌሎች የቤተክህነት አጋሮቻቸው በህቡዕና በግልጽ ይዘውታል፡፡
ከውጭ ደግሞ መምህር ዘላለም ወንድሙ፣ቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ፣ መምህር ተስፋዬ መቆያ፣ቀሲስ አስተርአየ ጽጌና መምህር አቡኑ እያስተባበሩ ይገኛሉ፡
በቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ያልተሰጠውና በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ፈፃሚና በአቡነ ጳውሎስ የተሾመው ኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን በአሜሪካ የማኀበረ ቅዱሳንን ህልውና ለማድረቅ የሚያደreገውን እንቅስቃሴ ለጊዜው ገታ አድርጎ ወደ ሀገረ ቤት በመዝለቅ ማኀበሩን ለመነቅነቅ እርምጃውን ጀምሯል፡፡
ግለሰቡ ማኀበሩን ለማፍረስ መሪ መንገዶች ናቸው ብሎ እንደ ዕቅድ ከያዛቸው ውስጥ ማኀበረ ቅዱሳን የሚታወቅበትን በግቢ ጉባኤ /ከፍተኛ የትም/ት ተቋማት የሚልፉትን ተማሪዎች ስለቤተክርስቲያናቸው በቂ እውቀት እንዲገበዩ፤ ሀገራቸውን ወዳድና በስነ ምግባር የታነጹ፤ በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ የቆሙ ብዙ ሺህ ምሁራንን ያፈራ በመሆኑ ይህን ዕቅድ ለመምታት የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች ማኀበረ በኩል ይህ የግቢ ጉባኤ ትምህርት እንዲሰጥና የመንፈሳዊ ኮሌጅ ምሩቃን ማኀበሩም ከመስከረም ጀምሮ ወደስራ እንዲገባና የተለያዩ ቅርንጫፍ ማዕከላትንም እንዲያዋቅር በፓትሪያሪኩ ታዟል::
የመንፈሳዊ ኮሌጅ ምሩቃን ማኀበር በቀን ብቻ የሚማሩ ተማሪዎች ያሉበት እንዲሆንና አብዛኛዎቹ የማኀበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊዎች ደግሞ በማታው መርሐ ግብር ትምህርታቸውን እየተከታተሉ በመሆናቸው ከቀን ተመራቂዎች ጋር አንድነት እንዳይኖራቸው እየጣሩም ነው
ይህ አስኳል የተሐድሶ ሕዋስ በጥድፊያ ወደዚህ ጉዳይ የገባበት ዋና ዋና ዓላማዎች ውስጥ የሚከተሉት እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ፡፡ የማኀበሩን ሕጋዊ ጥበቃ (ጥግ) ማሳጣት፣ ማኀበረ ቅዱሳን እንዲዘጋ ማድረግ የሚሉ ጭብጦችን ያነገበ ነው፡፡


  የጥፋት ምክሩ በፓትሪያሪኩና ጋሻ አጃግሬዎቻቸው ተጠንስሶ በሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ፊርማና ማህተም እንዲወጣና በአባ ገሪማ መልዕክተኛነት ፓትሪያሪኩ እንዳፈቅዱ ተደርጎ የመምሪያ ኃላፊው በጨለማ የተጠሩ ሲሆን በወከባ በቢሯቸው ያልተፃፈ ደብዳቤ እንዲፈርሙ ተደርጓል፡:
በቀጣይም በአሜሪየካ የሚገኙት ሰባኪያን ወንጌል ካልተፈቀደላቸውና ካልተጋበዙ በስተቀር የትም ቦታ እንዳያገለግሉ የሚል እቅድ ተነድፏል፡፡
በማግስቱ በእኝሁ የመምሪያ ኃላፊ ስምና ፊርማ የመጣውና ለተለያዩ የመንግስት አካላት የተፃፈው ደብዳቤ እንዲሚያመለክተው ኋላፊው የፈረሙት ደብዳቤ የመምሪያውን ይሁንታ ያላገኘና በወከባና በጥድፊያ በደንብ ሳያጤኑት የተፃፈ በመሆኑ ከመምሪያው ጸሐፈ ጀምሮ እስከ መንግስት አካላት እንዲያውቁት በግልባጭ አሳውቀዋል፡

ይህ መረጃ ማኀበሩ እንደደረሰው ፓትሪያሪኩና በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ካወቁ በኃላ በተናጥል የማደራጃ መምሪያ ኃላፊውን በመጥራት ስድብና ዛቻ አድርሰውባቸዋል፡፡ እንደ ምንጮቻችን ገለጻ ከሃላፊነታቸው ተነስተው የመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ሃላፊ ሆነዋል፡፡እነዚህ ግለሰቦች ጳጳሳትን በመከፋፈል በማኀበሩ ላይ የተለያየ አቋም እንዲኖራች ለማድረግ እየጣሩም ነው፡፡
ማኀበረ ቅዱሳን ነገሮች ኮሽ ባሉ ቁጥር ከመርበትበትና ያዙኝ ልቀቁኝ አይነት አካሔድ ከሚሔድ በሥሩ ያሉትን የስራ አመራርና አስፈፃሚ አባላት የመንግስት ፖለቲካዊ አጀንዳ ፈፃሚና አስፈፃሚ እንዳይሆኑና ሃይማኖታዊ ርዕይ ሰንቀው እንዲንቀሳቀሱ ጠቅላላ ጉባኤው ከወዲሁ የቤት ስራውን ቢሰራ ይበጀዋል ባይ ናቸው እነዚህ አባቶች፡፡
ያለበለዚያ ግን የማኀበሩ አመራር እየሄደበት ያለው የተሳሳተ አካሔድ እውነቱን ከመጋፈጥ ይልቅ በፍትፍት የአባቶችን ድጋፍ አገኛለሁ ብሎ መንቀሳቀስና የመቆያ መንገድ ለማበጀት የሚያደርገው ሩጫ ብዙ ርቀት የሚያስኬደው አይደለም፡፡ ከማኀበሩ ህልውና በላይ የቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ ህልውና ሊያሳስብና እንቀልፍ ሊነሳው ይገባል ይላሉ አባቶች፡፡ ልባችን ውስጥ ያለው ማኀበረ ቅዱሳንና ምሬት ላይ ያለው ማኀበረ ቅዱሳን የተለያዩ እንዳይሆኑ ማሰላሰያ ጊዜ አሁን ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ይደመድማሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመናፍቅነታቸው የሚታወቁት አባ ሰረቀ ብርሃንና በጋሻው ደሳለኝ አጣሪ ቡድኑ ምንፍቅና የለባቸውም የሚል ማረጋገጫ ሳያሳይ በደሞሳሳው መናፍቅ አይደሉም የሚል ደብዳቤ ሰጥቷቸዋል፡፡

No comments: