Wednesday, April 3, 2013

Friday, December 21, 2012

ሃይለማርያም ኢሳያስን አነጋግራለሁ ማለትና የኦህዴድ ዕጣ


ኢህአዴግ ከወትሮው በበለጠ አስመራ ላይና አስመራን ተገን ያደረጉ ተቃዋሚዎች አስመልክቶ የተንጠለጠሉ ጉዳዮችን አንድም በሰላማዊ መንገድ፣ አለያም በሃይል ለመቋጨት ፍላጎት እንዳለው ከተለያዩ ምንጮች ይሰማል። ይህንኑ መረጃ የሚያጠናክሩ መግለጫዎችና ዜናዎችም በቀጥታና በተዘዋሪ እየተደመጡ ነው። ድርድሩ የሚካሄደው ኦነግን ጨምሮ ከተለያዩ ድርጅት አመራሮች ጋር በተናጠል ስለመሆኑ ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ጠቁመዋል።

ኦነግንና ኢህአዴግን ለማስማማት ከላይ ታች የሚሉት የአገር ሽማግሌዎች የሚባለውን ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ኮሚቴ የሚመሩት ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅን ጨምሮ የቀድሞው የኦነግ አመራር አባቢያ አባጆቢር፣ የኢትዮጵያ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት የነበሩት ቄስ ኢተፋ ጎበናና ከሳቸው ጋር የሚሰሩት ኮሚቴዎች፣ በአሜሪካ የወንጌላዊት ሉትራን ቤ/ክ የአፍሪካ ብሔራዊ አገልግሎቶች ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ገመቺስ ቡባ ደስታ ከፊት ለፊት ረድፍ የተቀመጡ አሸናጋዮች መሆናቸው ብዙም የተሰወረ አይደለም::

ቄስ ኢተፋ ጎበናና ዶ/ር ገመቺስ “እርቅ ከፍትህ ጋር” የሚል የጸና እምነት ያላቸው ሲሆን “ትግል በቃኝ” በማለት አገር ቤት በመግባት ግጭትን በማስወገድ ላይ መሰረት አድርጎ የሚሰራ ተቋም ከዶ/ር ያዕቆብ ሃይለማርያም ጋር የመሰረቱት አባቢያ አባጆቢርና ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ የሚመሩት የአገር ሽማግሌዎች ቡድን እርቅ ላይ ስለሚከተለው መሰረታዊ እምነቱ በግልጽ የሚታወቅ ነገር የለም። የቅንጅት አመራሮች እንዲፈቱ በማድረግ ረገድ “ወርቃማ ገድል ፈጽሜያለሁ” የሚሉት ፕሮፌሰር ኤፍሬም በተለያዩ አካላት ተቃውሞ የደረሰባቸውና የ“ኢህአዴግ አፈ ቀላጤ” በሚል የሚያወግዟቸው ጥቂት አይደሉም።

ገመቺስ ቡባ ደስታ

መንግሥት ሲፈልግ “የለም” ሲያሻው “አሸባሪ” በማለት ከሚከሰው ኦነግ ጋር በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉት ድርድሮች ውጤት ሊያመጡ ያልቻሉበት ምክንያት አንዱ ሌላውን እምቢተኛ በማድረግ ከመወቃቀስ በዘለለ እርቁ ስለተበላሸበት ምክንያት ሁለቱም ወገኖች የሚስማሙበት እርግጠኛ ምክንያት አልተደመጠም።
አንዳንዴ ሶስት፣ ሲልም አራት ቦታ መሰነጣጠቁ የሚነገርለትን ኦነግ ከኢህአዴግ ጋር ለማስማማት በተለያዩ ወቅቶች የተደረጉ ድርድሮች ለመሰናከላቸው ትክክለኛው ምክንያት ባይቀርብም ዋናውና ትልቁ ችግር ግን የኦህዴድ ጉዳይ እንደሆነ ይነገራል። በኦህዴድ ውስጥ ድርድሩን የሚደግፉ ያሉትን ያህል የሚቃወሙትም አሉ። ስማቸው እንዳይጠቀስ የሚፈልጉ የኦህዴድ ሰዎች “ኦነግ ቢስማማና ህገ መንግስቱን አከብራለሁ ብሎ አገር ቤት ቢገባ የኦህዴድ እድል ምን ሊሆን ነው?” የሚል ጥያቄ ከሚያነሱት መካከል ይመደባሉ።

በተለያዩ መንገዶች ዋናውን ኦነግ አስማምቶ አገር ቤት የማስገባት ስራ እንደሚሰራ ማወቃቸውን የሚገልጹት ክፍሎች ጡረታ የወጡ የኦነግ ሰዎችን ፕሮፌሰር ኤፍሬም በማነጋገር ላይ መሆናቸውን ይጠቁማሉ። አባቢያም በተመሳሳይ ጀርመንና አሜሪካ ያሉ ወዳጆቻቸውን እያግባቡ እንደሆነ ይናገራሉ። የድርድሩ ደረጃ ምን ያህል እንደተጓዘ ባያብራሩም ድርድሩ ከሰመረ የተወሰኑ ሰዎች አገር ቤት ሊገቡ እንደሚችሉ ነው ያስታወቁት። መረጃው ምንጩ እንዳይታወቅ በመጠንቀቅ ዝርዝር ጉዳዮችን ያላብራሩት የኦህዴድ አባላት አሜሪካ ያሉ የኢህዴግ ዲፕሎማቶችና ወዳጆች በጉዳዩ ዙሪያ እየሰሩ እንደሆነ አመልክተዋል። ድርድሩ ከኦነግ ጋር ብቻም እንዳልሆነ ጠቁመዋል። እነዚህ ክፍሎች ቄስ ኢተፋ ጎበናና ዶ/ር ገመቺስ ስለሚመሩት እርቅ ግን ያሉት ነገር የለም።
ከፊሎቹ ደግሞ “ኦነግ ተደራድሮ በሰላም በምርጫ ለመወዳደር አገር ቤት ይገባል የሚለው ጉዳይ ላም አለኝ በሰማይ አይነት ነው” በማለት ከቶውንም ኢህአዴግ እንዲህ ያለ እብደት ውስጥ እንደማይገባ ይከራከራሉ። ምናልባትም በሰላም እንደሚያምን፣ ለእርቅ የተዘጋጀ እንደሆነ ለውጪው ዓለም ለማሳመን ካልሆነ በቀር።


እነዚህ ክፍሎች የማይሸሽጉት አንድ እውነት ግን አለ። ኢህአዴግ ቁልፍ የኦነግ ሰዎችን መማረክ ይፈልጋል። እነዚህ ቁልፍ ሰዎች በድርድር ተማርከው ወይም ተስማምተው አገር ቤት ከገቡ ኦነግ በተደጋጋሚ ከደረሰበት የውስጥ ችግር ጋር ተዳምሮ ከደጋፊዎቹ ጋር ይለያያል ይላሉ። ለዚህ ጠንካራ ነገር ግን ቅዠት የሚመስል ትንታኔያቸው የሚያቀርቡት ማስረጃ አስደንጋጭ ይመስላል።

ለጎልጉል እንደወትሮው ስማቸው እንዳይጠቀስ በማስጠንቀቅ ማብራሪያቸውን የሚያቀርቡት ክፍሎች፣ ታዋቂ የሆኑትን የኦነግ ሰዎች ለማጥመድ ኢሳያስ አፈወርቂ አንደኛው አማራጭ ናቸው። ሰሞኑን በግምገማ ተወጥሮ የከረመው ህወሃት በሃይል ኢሳያስን የማስወገድ አቋም እንዳለው ጠቅሶ ኢንዲያን ኦሽን ኒውስ ሌተር የጻፈውን እንደሚስማሙበት የሚጠቅሱት ክፍሎች በየትኛውም መመዘኛ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ወገን የሃይል እርምጃ ቢያጣድፋት የመመከት አቅም አይኖራትም። ይልቁኑም ኦፕሬሽኑ አጭር፣ የማያዳግም፣ ኢሳያስንና አብረዋቸው ያሉትን በሙሉ ሊጠራርግ የሚችል ይሆናል። በዚህ መነሻነት ኢሳያስ ከመለስ ሞት በኋላ ያለውን ህወሃትን እንደፈሩት አስረግጠው ይከራከራሉ።

ሃሳባቸውን ሲያጠናክሩ፣ ከወራት በፊት ከኢትዮጵያ በኩል በተደጋጋሚ ድብደባ የተፈጸመባቸው ኢሳያስ የደረሰባቸውን ቁሳዊና ሰብዓዊ ጥፋት ለተባበሩት መንግስታት በክስ መልክ ከማቅረብ የዘለለ የወሰዱት ርምጃ የለም። የወትሮው ኢሳያስ እንኳን ተነክተው እንዲያውም ጸብ የሚሸታቸው እንደነበሩ የሚጠቁሙት ክፍሎች አስመራ ከተማ ጡረታ የወጡ የቀድሞ አዛውንት ታጋዮችን ከማስታጠቅ የዘለለ እርምጃ አለመውሰዳቸው የፍርሃታቸውን መጠን አመላካች መሆኑን ያሳያሉ። ተጨማሪ የማጠናከሪያ ማስረጃም ያቀርባሉ።

“ስለሆነም” ይላሉ የሚያውቁትን የግምገማ ማጠቃለያ ሲያቀርቡ “ኢሳያስ ከኢትዮጵያ ወገን የሚቀርብላቸውን የሰላም ድርድር አልቀበልም የሚሉበት ምክንያት የላቸውም። ሊሉም አይችሉም። ለድርድር ሲቀርቡም በቀድሞው ኃይል፣ ምንጩና መነሻው ኢትዮጵያ ላይ ማንጸባረቅ በሚፈልጉት ግራ የሚያጋባ የበላይነት ስሜት ሊሆን አይችልም” በማለት ኢሳያስ ወደ ድርድር የሚመጡበትን አስገዳጅ ሁኔታዎች ያስቀምጣሉ።
ኢሳያስ ለድርድር ከተቀመጡ የመጀመሪያው ጥያቄ ተቃዋሚዎችን ወደ ሰላም እንዲመጡ ማስገደድ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስትም በተመሳሳይ እርምጃ ይወስዳል። ቀጣዩ የባድመ ጉዳይ አቶ በረከት ስምዖን እንዳሉት “የኢትዮጵያ አይደለም” ይባልና በድንበር ማካለሉ መጠነኛ የሞራል መጠበቂያ ሽግሽግ ተደርጎ ይጠናቀቃል የሚል መደምደሚያ ይሰጣሉ።

“በየቀኑ በርካታ ወታደሮች የሚኮበልሉባቸው ኢሳያስ የሚቀርቧቸውን የተቃዋሚ ቁልፍ ሰዎች በማደራደር ስም ኢህአዴግ እጅ እንዲወድቁ ያደርጓቸዋል። ይህ የማይቀር እውነት ነው። የውጪ አገራትም ድጋፍ አለበት” የሚሉት ክፍሎች “ከዚህ የተለየ ጉዳይና ድርድር ካለ ኦህዴድ እንዲፈርስ ማድረግ ነው። ይህንን ማድረግ ደግሞ እብደት ነው። ይደረግ ከተባለም ስርዓቱ ያከትምለታል” ባይ ናቸው። እነዚሁ ክፍሎች አቶ በረከት በቅርቡ ስለኤርትራ የተናገሩትንና ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ አስመራ ድረስ ለድርደር እንደሚሄዱ መናገራቸውን የቅርቡ ጊዜ ማጣቀሻ አድርገው ያሳያሉ።

ኢህአዴግ ከወትሮው በተለየ የእርቅና የሰላም ድርድር ላይ እየሰራ ባለበት በአሁኑ ወቅት አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር አስመራ ሄደውም ቢሆን ለመደራደር ቢጠየቁ ፈቃደኛነታቸውን ያለ አንዳች ማቅማማት እንደሚያሳዩ መግለጻቸው ኢሳያስን ወደ ድርደር ለመጋበዝና ለማማለል እንደሆነ ተደርጎ ተወስዷል።

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከአልጃዚራ እንግሊዝኛ ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሲናገሩ “አስመራ ሄደህ ከኢሳያስ ጋር ተቀምጠህ ትደራደራለህ? ብለሽ ብትጠይቂኝ” አሉና ራሳቸውን ጠየቁ። “አዎ! ነው መልሴ” በማለት ለራሳቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ። አስከትለውም “በርግጥም አደርገዋለሁ” በማለት ማረጋገጫ ሰጡ።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር

ጠያቂዋ የቀድሞው መሪ አቶ መለስ ሊያደርጉት እንደማይችሉ ስትጠቁም፣ አቶ መለስ ከሃምሳ ጊዜ በላይ አስመራ ሄደው ለመደራደር ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጥያቄ ማቅረባቸውን በማስታወስ ምላሽ የሰነዘሩት አቶ ሃይለማርያም፣ ድህነትን መዋጋት ትልቁ ጉዳይ እንደሆነ በመግለጽ “ሁለታችን ብንስማማ እጅግ ታላቅ ውጤት ይኖረው ነበር” ያሉት።

የጎልጉል ምንጮች እንደሚሉት ደቡብ ሱዳን በውጤት አጠናቅቀዋለሁ የምትለው የሁለቱ ድርጅቶች (ህወሓትና ሻዕቢያ) የሰላም ድርድር ተግባራዊ ይሁንም አይሁን፣ በሌላ አሁን ይፋ ሊያደርጉት በማይፈልጉት አካል አማካይነት የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ ይሆናል።

የኦህዴድ ሰዎች ያቀረቡትን ማብራሪያ የሚያጣጥሉ ክፍሎች በበኩላቸው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከቀድሞው በተሻለ ዲፕሎማሲያቸውን አስተካክለዋል። ይህም ባይሆን ህወሃት ኢሳያስን ተጭኖና ተከራክሮ ያሸነፈበት አንድም ጊዜ ስለሌለ ወደፊትም የተለየ ነገር አይመጣም ይላሉ።

በስልጣን ተዋጽኦና በሃላፊዎች ስብጠር ችግር ገብቶታል የሚባለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የመዋጋት ፍላጎቱ እንደቀድሞው እንዳልሆነ የሚያመለክቱት እነዚህ ክፍሎች “ጦሩ አስመራ ለመግባት እየተንደረደረ በነበረበት ሰዓት በተፈጸመበት ክህደት አዝኗል። እንደ ዘመቻ ጸሃይ ግባት በወኔና በእልህ የመዋጋት ፍላጎት የለም። ኢህአዴግም ይህንን ስለሚረዳ ጦርነትን በፍጹም አይሞክርም። ችግር ከተፈጠረ ቀዳሚው ተጎጂ ህወሃት ነው። ህወሃት ላይ የሚደርሰው ጉዳት ደግሞ ህልውናን አስከማጣት ያደርሰዋል። በዚሁ ፍርሃቻ የሰላም ስምምነት ቢኖር እንኳ ኢህአዴግ እንደለመደው ብዙ በመስጠት ጥቂት ተቀብሎ ሊስማማ ይችል እንደሆነ እንጂ አያተርፍም” የሚል መከራከሪያ አላቸው።
ኢሳያስ በተደጋጋሚ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን እንዲሁም በቅርቡ ካናዳ ጥገኝነት ጠየቁ ሲባሉ በቅርብ የሚያውቋቸው “የኢሳያስ ልጅ አይከዱም” በማለት የተከራከሩላቸው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አሊ አብዶ አሰብን አስመልከቶ “የኢትዮጵያ ህዝብ በአሰብ ወደብ የመጠቀም ሙሉ መብት አለው” ማለታቸው ውስጥ ውስጡን ለሚካሄደው ስምምነት አመላካች እንደሆነ ገለልተኛ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

ሌላው የሚያነሱት መከራከሪያ አቶ መለስ ያደረጁዋቸውና ኢትዮጵያ ውስጥ የስደት መንግስት አቋቁመው የኢሳያስን ውድቀት የሚጠባበቁት የኤርትራ ተቃዋሚዎችን አደረጃጀት ነው።ተቃዋሚዎቹ በውስጣቸው ያቀፏቸው ብሄርን መሰረት ያደረጉ ፓርቲዎች ወደ ስልጣን ከመጡ በኤርትራ ሊከሰት የሚችለው አደጋ ለሁሉም አገር ወዳድ የኤርትራ ዜጎች ስውር አይደለም።በዚህም ሳቢያ ኢሳያስ ከለቀቁ ቀጣይዋ ኤርትራ የብሄርና የጎሳ ፖለቲካ የሚፈለፈልባት ልትሆን ትችላለች የሚለው ስጋት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን ጨምሮ በየትኛውም ቦታ የሚገኙ ኤርትራውያን አገራቸውን መስዋዕትነት ከፍለው ለመከላከል ዋናው ምክንያታቸው ነው። በዚህም ምክንያት ግጭት ከተነሳ በአጭር ጊዜ የሚፈጸም አድርጎ መታየቱን ይቃወማሉ። ኢህአዴግም ይህንን እንደሚረዳ ያስገነዝባሉ።
ህወሓት/ኢህአዴግ የሚፈልገውና የሚያሳስበው ነገር ካለ በሱዳን እንዳደረገው መሬት በመስጠት ጭምር እንደሚደራደር ያመለከቱት አስተያየት ሰጪዎች “በሰላማዊ መንገድ የኤርትራና የኢትዮጵያ ጉዳይ በዘንድሮው ዓመት አንድ ደረጃ ላይ የሚደርስ ይመስለናል” በማለት ቅድመ ግምታቸውን ያኖራሉ። ኤርትራ ላይ የከተሙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎች ድርድርም ሆነ ማግባባት ካለ ከወዲሁ በመጠንቀቅ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ይመክራሉ።
የሃይለማርያም ደሳለኝን የዕርቅ ጅማሮ ጥቅምና ጉዳት ከሌላ አንጻር የሚያብራሩ ደግሞ አቶ መለስ በአገር መክዳት ከተወነጀሉበት የባድመ ጦርነት በኋላ ሌላ የትግራይ ባለሥልጣን ወደ ኤርትራ ሄዶ ከኢሳያስ ጋር እጅ ቢጨባበጥ በትግራይ ተወላጆች ዘንድ የሚፈጥረው ስሜት ጀምሮ በህወሓት ውስጥ ሌላ ህንፍሽፍሽ (ክፍፍል) ከማስነሳቱና ከሻዕቢያም በኩል የኤርትራን ስነልቦና ከመጠበቅ አኳያ አቶ ሃይለማርያም ጥሩ ፊት ሊኖራቸው ስለሚችል የጠ/ሚ/ሩ ሥልጣን በህወሓት ከመወሰዱ በፊት ወቅቱ ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሯል ይላሉ፡፡
ከሰባ ሺህ በላይ ወገኖችን ሕይወት የቀጠፈው የባድመ ጦርነት መንስዔ የሆነው የድንበር ውዝግብ እስካሁን እልባት አላገኘም። የተባበሩት መንግስታት የድንበር ኮሚሽን ባድመን ለኤርትራ እንድትሆን አድርጎ ተቀብሏል፤ ሄግ ያስቻለውን ችሎት የፈረደውን ውሳኔ ኢትዮጵያ ተግባራዊ በማድረግ ባድመን ለቃ እንድትወጣ ብትታዘዘም አሁን ድረስ መሬቱን የምትቆጣጠረዋ ኢትዮጵያ መሆኗ ይታወሳል። ከዚህ ዘግናኝና ታላቅ ሰብዓዊ ቀውስ ካስከተለ ጦርነት በኋላ ከኢሳያስ ጋር ለመነጋገር ሃይለማርያም ኤርትራ ከሄዱ ከጦርነቱ በኋላ ኤርትራን የሚረግጡ የመጀመሪያ መሪ ይሆናሉ።

በሌላ ተመሳሳይ ዜና ኦነግን ለማስማማትና ወደ ድርድር ለማቅረብ ፕ/ር ኤፍሬም ኖርዌይ መታየታቸውን ተከትሎ ኢህአፓ ለኖርዌይ መንግስት የተቃውሞ ደብዳቤ መላኩን አስታውቋል። ድርጅቱ በደብዳቤው የኖርዌይ መንግስት እንዲህ ካለው ተቃዋሚዎችን የሚጎዳ እንቅስቃሴ ከመፈጸም እንዲትቆጠብ በላከው የተማጽኖና የማሳሰቢያ ደብዳቤ አምባገነኖችን በመርዳት የሚደረገው ድጋፍ ሊቆምና ለዴሞክራሲ መበልጸግ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አመልክቷል።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ 
 
ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

የሹም-ሽሩ ምስጢርና ዋናው ጠቅላይ ሚኒስትር!


በሰሎሞን ተሰማ ጂ. (semnaworeq.blogspot.com)
ባለፈው ሐሙስ በተደረገው የኢህአዴግ/ወያኔ የካቢኔ ሹም-ሽር ላይ በርካታ አስተያየቶች በመደመጥ ላይ ናቸው፡፡ ሆኖም የበርካቶቹ አስተያየትና ትንተና እዚህ ግባ የማይባልና፣ በወያኔዎች አማርኛም “ውኃ የማይቋጥር” ሆኖ ስላገኘሁት፣ የኔን አስተውህሎት ላቀርብ ወደድኩ፡፡ በቅድሚያ ግን፣ በሀገር ውስጥ ያሉት የተቃዋሚ ፖለቲካ ማኅበሮች/ፓርቲዎች መሪዎች እየተቀባበሉ የሚደጋግሙት ነገር ያው የተለመደውን ነው፤ “ሹመቱ ሕገ መንግሥቱን የተከተለ አይደለም!” ምናምን የሚል ወቀሳ አይሉት ትችት፣ እንዲያው የንፉግና የፈሪ ጩኸት ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎቹን መሪዎች ወያኔ ደጋግሞ አጥጋቢ አማራጭ የላችሁም የሚላቸው ለምን እንደሆነ፣ ብዙዎቹ አሁንም አልተገለጠላቸውም፡፡ መቼ “ተገለጠ/ቡድሀ!” ብለው እንደሚጮሁ አላውቅም፤ በተስፋ ግን እንጠባበቃለን፡፡
ወደዋናው ጉዳያችን እንመለስ፡፡ ኢሕአዴግ/ወያኔ የሰሞኑን ሹም-ሽር ሲያደርግ ለሕዝቡ አዲስ ነገር አልሆነበትም፡፡ አዲስ ነገር የሆነባቸው ካሉም ኢሳት ቴሌቪዥን በነሐሴ 2004 ዓ.ም ያወጣውን መረጃ ያላነበቡትና ወቅታዊ የፖለቲካ ጥንቅሮችን የማይከታተሉት ወገኖች ብቻ ናቸው፡፡ በሀገር ጉዳይ (በወል ቤታችን ጉዳይ ላይ እስከመቼ ድረስ ቸልተኛና ገለልተኛ ሆነው እንደሚቀጥሉ ባይገባኝም) ላይ ቸለል የሚሉት ወገኖች ናቸው፡፡ ከዚያ ወጭ ያሉትና የወቅቱን የሕወሀት-ወያኔን መቅነዝነዝ ሰበብ ያልተረዱት ብቻ ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ነፍስ ፖለቲከኛ ሆና በመገኘት ፈንታ “መሲሐዊት” ለመሆን እየተንደፋደፈች መሆኗን ወያኔዎች መረዳታቸው ነው፡፡ በመሆኑም ከነበሯቸው ብዙ ብዙ አማራጮች መካከል የሦስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ሹመት አጸደቁ፡፡
የፓርላማውን ስርጭት ለተመለከተው ሰው ሁለት የሚደንቁ አልቦ-ቋንቋ እንቅስቃሳችን ጠቅላይ ሚኒስትሩና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን አሳይተዋል፡፡ የተሹዋሚዎቹን ስም ዝርዝር ሲያነብ የነበረው ኃይለ ማርያም ደሳለኝ (The Mimic Man)፣ መለሰ ዜናዊኛ ማስኩ/ጭንብሉ ጠፍቶበት ሲኮለታተፍ ነበር፡፡ ምናልባትም በሥራ ብዛት ሰበብ ይህንን የሚያህል ድርጅታዊ ውሳኔ ሲወሰን በስብሰባ ላይ አልተገኘም ነበር ይሆናል፡፡ ጎበዞቹ የወያኔ አርክቴክቶች ውሳኔያቸውን እንዲያነብ አዳራሹ ውስጥ ከገባ በኋላ ነው የሰጡት፡፡ የተሹዋሚዎቹን ስም ዝርዝር ሲያነብ ከፍተኛ የሆነ ቃና-ቢስነት ይታይበት ነበር፡፡
ተሹዋሚዎቹ ቃለ መኻላቸውን ከፈፀሙ በኋላ ደግሞ አቶ ደመቀ መኮንን ፊቱን አቀጭሞ ለማጨብጨብ እንኳን ሲጠየፍ ላየው፣ በሥራ ብዛት የተነሳ፣ እርሱም ይህንን ከፍተኛ ድርጅታዊ ውሳኔ ሳይሰማ እንደቀረ ያጋፍጣል፡፡ ያም ሆኖ፣ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በእኩልነት ላይ ያልቆመው የኢሕአዴግ/ወያኔ ካቢኔ በስመ ክላስተር፣ ቀደም ብሎ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አዲሱ ለገሰ አስይዞት የነበረውን የግብርናና ገጠር ልማት ኃላፊነት ሸርሽሮ ልፍስፍስ ክላስተር አደረገው፡፡ በአቅም ግንባታው ሚ/ር ተፈራ ዋልዋ ተይዞ የነበረውን ሸርሽሮ ለአቶ ሙክታር ሰጠው፡፡ በዶ/ር ካሱ ኢላላም ተይዞ የነበረውን የመሠረተ ልማት ሚኒስትርነት ሥልጣን አዘምኖና ደራርቦ፣ በዚያም ላይ የቴሌኮሙን ደሕንነት ከነማዕከላዊው ደሕንነት ተያያዥ ኃላፊነቶች ለዶ/ር ደብረ ፂዮን ሰጠው፡፡ እንደተለመደው፣ ከፈረንጆቹ ጋር የመሞዳሞዱን ጉዳይ ለይስሙላ ለኃይለ ማርያም ሰጥተው ሲያመነቱ ከቆዩ በኋላ፣ መልሰው “በስዩም መስፍን ርስት፣ ዶ/ር ቴድሮስ አድኀኖም ሆይ-ግባበት!” አሉት፡፡
የሹምሽሩ ፖለቲካዊ አንደምታዎች ምንድናቸው?
ዋነኛውና የመጀመሪያው ነጥብ የአቶ ኃይለ ማርያም ባሕሪ ከተሞክሮ መታወቁ ነው፡፡ በ1993ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኃላፊነት ሲሠራ ሳለ መጠነኛ የተማሪዎች ነውጥና ግርግር ሲፈጠር፣ መቆጣጠር ተስኖት ወደሃይማኖታዊነቱ አዘነበለ፡፡ መራሹ ወያኔም፣ በራሱ መንገድ የተማሪዎቹን አመጽ መረሸው፡፡ ከአባተ ኪሾም ቀጥሎ በደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድርነት እየሠራ ሳለ፣ የሲዳማዎችና የከንባታዎች አመጽ ሲነሳ፣ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እንደተለመደው መቆጣጠር ተስኖት መልቀቂያ ሁሉ ሊያስገባ እያመነታ እንደነበር የቅርብ ሰዎቹ ይመሰክራሉ፡፡ በ1998 ዓ.ም በኋላም ቢሆን የሚያስጨንቁ ችግሮች ሲከሰቱ መውጫ ቀዳዳ የሚፈልገውን ኃይለ ማርያም፣ አቶ መለሠ ዜናዊ እንዴት mimic man መሆን እንደሚችል እያረሳሳ ነበር ያቆየው፡፡ ስለዚህም፣ አቶ ኃይለ ማርያም የኋሊት የፈረጠጠ እንደሆ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ሥልጣን በታሪክ አጋጣሚ ኃይለ ማርያም ላይ እንደወደቀው ሁሉ፣ “ደግሞ አቶ ደመቀ መኮንን እጅ ሊወድቅ አይደለምን?” ብሎ ያልሰጋ የወያኔ ከፍተኛ አመራር አልነበረም፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ሥልጣንም በአቶ ደመቀ መኮንን እጅም እንዳይወድቅ የማይፈልግበት ሁለት ምክንያቶች አሉ፡፡ አንደኛው ምክንያት የዘሩ ጉዳይ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የሃይማኖቱ ጣጣ ነው፡፡ ሁለቱንም ነጥቦች ለጥቆማ ያህል እናንሳቸው እንጂ በዝርዝር እንዳናስቀምጣቸው እንፈልጋለን፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ለወያኔ አጀንዳ መመቸት ስለሚሆን ነው፡፡ ለማንኛውም፣ የአቶ ደመቀ መኮንን አሊን ምርጫ፣ በሁለቱ መሥፈርቶች ምክንያት አደገኛ የሆነ ችግር እንደሚያስከትል በዝግ የወያኔ ስብሰባዎች ላይ ተደጋግሞ ተወሳ፡፡ በመጨረሻም፣ ሦስት የመጠባበቂያ እቅዶች ተነደፉ፡፡ አንደኛ፣ በውስጥ የስልጣን ውክልና የሚብላላውን ኦሕዲድን ለማስተንፈስ አቶ ሙክታርን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ማዕረግ ለመሾም፤ ሁለተኛ፣ አቶ ደብረ ፂዮንን በፊታውራሪነት አስቀድሞ፣ የአቶ ኃይለ ማርያም ባሕሪያዊ ችግር ቢፈጠር እንዲተካው ማዘጋጀት፤ እና ሦስተኛም፣ ምናልባት ደብረ ፂዮንን ሕዝቡ ባይደግፈው/If not Popular/፣ ከአቶ አርከበ እቁባይ ቀጥሎ ሕዝባዊ አመኔታ እያገኘ ያለውን ቴድሮስ አድኃኖምን በመጠባበቂያ ዕቅድነት ይዞ መንቀሳቀስ የሚሉ ነበሩ፡፡
ስለሆነም የሹም ሽሩ ዋነኛው አንደምታም፤ ምናልባት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በርትቶ ኃላፊነቱን ከተወጣ እሰየው፤ ካልተወጣ ግን በነሐሴ 2004 እና በመስከረም 2005 ዓ.ም፣ በድሕረ-መለሠ ዜናዊ ወቅት የተፈጠረውን የሕወሀት-ወያኔ የተተኪ መሪዎች ችግር ለመፍታት ነው፡፡ በመሆኑም፣ ሦስቱ የወያኔ እህት ድርጅቶች አንድ አንድ እጩዎችን ሲያዘጋጁ (ለዚያውም የፖለቲካ ውሳኔዎቻቸውና የሥልጣን ምሕዳራቸው ልፍስፍስ በመሆኑ የተነሳ አፈጻጸማቸው ደካማ እንዲሆን ሆን ተብሎ ተዘይዷል)፣ ሕወሀት-ወያኔ ግን ሁለት እጩዎችን አዘጋጅታለች፡፡ ለዚያውም በጉልሕ ሙሉ ሥልጣናቸውና አፈጻጸማቸው ሳይቀር እንዳይስተጓጎል ተብሎ የፋይናንስና የኤኮኖሚውን ክላስተር ከነደሕንነቱ፣ ከነውጭ ጉዳይ ጽ/ቤቱ፣ ብሎም ከነመከላከያ ሠራዊቱ ይዘው እንዴት አፈጻጸማቸውና ሥልጣናቸው ሊቀጥል አይችልም?
እንግዲህ ወደማጠቃለያ ሀሳባችን ተዳርሰናል፡፡ እንደምታስታውሱት ኢሕአዴግ የአራት ድርጅቶች ጥምር ፓርቲ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ሥልጣን እስካሁን ሦስት ፓርቲዎች ተቋድሰውታል፡፡ ኢሕዴን/ብአዴንን ወክሎ አቶ ታምራት ላይኔ ከሰኔ 1983 ዓ.ም እስከ መስከረም 1987 ዓ.ም ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበር፡፡ ከ1987 መስከረም ወር ጀምሮ እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም አቶ መለሠ ዜናዊ ሕወሀት/ወያኔን ወክሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበር፡፡ አሁን ከመስከረም 9 ቀን 2005 ጀምሮ ደግሞ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ደሕዴድን ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ተረክቧል፡፡ ሁሉም ነገር በተያዘለት መርሀ ግብር መሠረት ከሄደም፣ ቀጣዩ የወር ተረኛና ጠቅላይ ሚኒስትር ከኦህዴድ መሆን ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን፣ የአማሮችና የኦሮሞዎች ጠቅላይ ሚኒስትርነት የማይዋጥለት የወያኔ ከፍተኛ አመራር መልሶ ለመጠቅለል የሚያስችለውን የማሳሳቻ /camouflage/ ዕቅድ ነድፏል፡፡ በዚህም እቅድ መሠረት፣ ሕወሀት-ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ከደቡብ እንዳይሆን ለመከራከር ከመሞከሩም በላይ፣ እድሉን ክፍ አድርጎ ለመገኘት ሲል በሁለት እጅ ብልጫውን ለመውሰድም ተዘጋጅቷል፡፡ ኦሕዲድ በሙክታር ሊወከል ቢችልም ቅሉ፣ መስከረም 2005 ላይ ሱፊያን አሕመድ የገጠመውን ጽዋ ይጎነጭ ይሆናል፡፡ አቶ ደመቀ መኮንንም ልክ እንደቀዳሚዎቹ የብአዴን ም/ጠቅላይ ሚኒስትሮች አቶ ተፈራ ዋልዋና አቶ አዲሱ ለገሰ ዓይነት “እርም ጠቅላይ ሚኒስትርነት!” ብሎ ይቀራል ማለት ነው፡፡ በማካያውም፣ ሕውሀት በዶ/ር ደብረ ፂዮንና በዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም አማካይነት ከብአዲንና ከኦሕዲድ ተወካዮች ጋር ሲወዳደሩ ሃምሳ-በመቶ (50%) እድል ይኖራቸዋል ማለት ነው፡፡ ይህንን እድል ማን ይሠጣል? ደንበኛ የማሳሳቻ /camouflage/ ዕቅድ ነድፏል ማለት እንዲህ ነው፡፡ (ቸር እንሰንብት!)
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
December 6, 2012

የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥ ማነው? (እየሩሳሌም አርአያ)


በከፍተኛው ፍ/ቤት ዳኛ ሆነው ለረጅም ዓመት አገልግለዋል፤ ከዚያ ከለቀቁ በሁዋላ በጥብቅና ሙያ እየሰሩ ይገኛሉ። ታዋቂው የህግ ባለሙያ አነጋጋሪ በሆኑ የኢህአዴግ የፈጠራ ክሶች ዙሪያ ለተከሳሾች ጥብቅና በመቆምና በድፍረት በመሙዋገት ይታወቃሉ። በ1997 ከአንድ የፈጠራ ክስ ጋር በተያያዘ ለተከሳሾች ጥብቅና ቆመው ነበር፤ በፌደራል ጠ/ፍ/ቤት በተሰየሙ ዳኛ ተብዬዋች ተግባር ክፉኛ የተበሳጩት እኚህ የህግ ባለሙያ በወቅቱ እንዲህ አሉኝ፥
« በንጉሱ ዘመን ነው፤ በአ.አ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ልንመረቅ ሽር ጉድ እንላለን። የምንወደው የህግ መምህራችን የኛን ሁኔታ ታዝቦ ኖሮ…አንድ ጥያቄ አቀረበልን፤ “ አሁን ሳያችሁ በደስታ እንደተዋጣችሁ ነው፤ በመመረቃችሁ ደስተኛ ናችሁ ማለት ነው?... “ ሁላችንም በጥያቄው ተገርመን ..< እንዴት መምህር?..በጣም ደስተኞች ነን ፤ > አልነው። ደግሞ ጠየቀን ፥ “ ሁላችሁም ደስተኞች ናችሁ?”..ሲለን..< አዎን ደስተኞች ነን > አልነው በአንድ ድምፅ። በጣም አዝኖ እንዲህ አለን ፥ < ሕግ በሌለበት አገር ህግ ተምራችሁ ..ሕግ የምታስፈፅሙ ይመስል፥ እንዲህ መደሰታችሁና መመፃደቃችሁ ታሳዝናላችሁ.!>… ዛሬ የበለጠ የመምህራችን ንግግር ታወሰኝ፤ እውነትም ሕግ በሌለበት አገር…» ሲሉ ታዋቂው የህግ ባለሙያ ያወጉኝን ለመጣጥፌ መንደርደሪያ ማስቀደሜ ያለምክንያት አይደለም።
ጠ/ሚ/ር ተብለው የተቀመጡት ሃ/ማሪያም ደሳለኝ የጦር ሃይሎች ጠ/አዛዥነቱ ስልጣን አልተቀበሉም። ቀደም ሲል ይህ ስልጣን በአቶ መለስ እጅ ነበር። እንዲያውም የከፍተኛ ጄኔራሎች ሹመት በተመለከተ ቀደም ሲል የነበረውን ሕግ በመሻር ስልጣኑን ጠቅልለው የያዙት አቶ መለስ ነበሩ። ይህ የተደረገው ከ1993ዓ.ም ወዲህ ነበር፤ ከዚያ በፊት ግን የጦር አዛዦችን ሹመት የሚያቀርበው ጠ/ሚኒስትሩ ሲሆን የሚያፀድቀውና የሚሽረው ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ነበር። ፕ/ት ነጋሶ ከስልጣን ለመልቀቅ የወሰኑበት አንዱ ምክንያት ይህው ነበር። ከሳቸው እውቅና ውጭ ጠ/ሚ/ሩ ጄኔራሎችን በማባረራቸው እንደነበር ይታወሳል። ከዛ በሁዋላ አቶ መለስ ስልጣኑ ሙሉ በሙሉ የጠ/ሚ/ሩ እንዲሆን የሚያስችል ህግ አውጥተው አረፉት። የሚሽሩትም የሚሾሙትም እርሳቸው ሆኑ።
ባለፈው ጊዜ ጠ/ሚ/ር ሳይኖር 34 ጄኔራሎች መሾማቸው ተነገረ፤ አስገራሚና አነጋጋሪነቱ እንዳለ ሆኖ ለዚህ የተሰጠው መልስ ይበልጥ አስቂኝ ነበር። « ቀደም ሲል በጠ/ሚ/ሩ የተዘጋጀ ነው» ብለው በረከት ተናገሩ። ከተሾሙት መካከል መለስ ለሹመት ለአፍታ ሊያስቡዋቸው የማይችሉ መኮንኖች መኖራቸው የበረከት መልስ ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ታዛቢዋች በወቅቱ አስተያየት የሰጡበት ነው።
አሁን ደግሞ « የጦር ሃይሎች አዛዡ ማነው?» ተብሎ ቢጠየቅ መልስ የለም። ሕጉን እንቀበል ቢባል እንኩዋን ስልጣኑ በጠ/ሚ/ር ሃ/ማሪያም እጅ አይደለም። አሁን አገሪቱዋን የሚመራው የጦር ሃይሉ ጠ/አዛዥ ማነው? የሚል ጥያቄ ቢነሳ ተጨባጭ መልስ መስጠት አይቻልም። ስልጣኑ በዘፈቀደ የተለያዩ የሕወሓት ጄኔራሎች እና ባለስልጣናት እንዲሁም ከመጋረጃው ጀርባ ባደፈጡ የድርጅቱ ባለስልጣናት እጅ እየተሽከረከረ እንዳለ መረጃዋች ይጠቁማሉ። ለመጥቀስ ካስፈለገ ባለፈው ወር በሳሞራ ቀጭን የስልክ ትዕዛዝ የተነሱት ጄኔራል…በአስገራሚ ሁኔታ እንዲመለሱ የተደረገው ከጀርባ ሆነው አንድ ቡድን በሚያሽከረክሩት ስብሃት ነጋ እንዲሁም ሌሎች ተከታዮቻቸው ርብርብ ነው። በተነሱት ጄ/ል የተተኩት እንዲነሱ የተደረገውም በዚሁ ቡድን ጣልቃ ገብና ሕገ-ወጥ ውሳኔ ነው። ሕግ፡አዋጅ…የሚባል ጨርሶ አይሰራም!! ከዚህ በተጨማሪ 3 ጄኔራሎችን ጨምሮ በርካታ የበታች መኮንኖች ታግደው..ውሳኔ እየጠበቁ ነው፤ ከታገዱት ከኦህዴድ ወገን ይበዛሉ። ይህ ሁሉ እየተደረገ ያለው በጄ/ል ሳሞራና ከሳቸው ጋር በተሰለፉ የቡድን አባላት ሲሆን በተቃራኒ ያለው ቡድንም የራሱን የማባረርና የማስመለስ ድራማውን ገፍቶበታል። ይህ ሁሉ የሚከወነው የሃ/ማሪያምን በአዋጅ የተቀመጠ ስልጣን በአደባባይ በጡንቻ በመውሰድ ወይም በመግፈፍ ነው። ጠ/ሚ/ሩ < ለምን?..እንዴት.. ከኔ እውቅና ውጭ..? > ብለው ለመጠየቅ ይቅርና የሚያስቡት አይመስልም። አይተው እንዳላዩ መሆንን መርጠዋል።
ከዚህ ይልቅ የመለስን «ካባ» አጥልቀው « ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አስመራ ሄጄም ቢሆን እነጋገራለው፤ እደራደራለው» ማለቱን ተያይዘውታል። ይህም ቢሆን የርሳቸው ውሳኔ ሳይሆን ከጀርባ ያለው ሃይል የቆየ ፍላጐትና እመነት ነው። ብዙ ወገኖችን ያስገረመው ጉዳይ ባለስልጣናቱ ለሻዕቢያ ባለስልጣናት የሚያቀርቡት ልምምጥ የሚታይበት የድርድር ጥያቄና ተማፅኖ፥ በአገር ውስጥና በውጭ ላሉ ተቃዋሚዎች ለአንድ አፍታ ሊቀርብ ቀርቶ ያለመታሰቡ ነው። ከዚህ ይልቅ « ድርድር አይታሰብም» ከሚለው አንስቶ..« የሻዕቢያ
ተላላኪዎች፡ ፀረ-ሰላም ሃይሎች..አሸባሪዎች..» የሚል ያልተጨበጠ ታርጋ እየለጠፉ መወንጀል፡መዝለፍና እስር ቤት መወርወርን ስራዬ ብለው የገፉበት ተጨባጭ እውነታ ነው የሚታየው። የገዢዎቹ ሃሳብና ድርጊት እንደሚጋጭ የሚሳየው « ሻዕብያን ፀረ ሰላም ሃይሎችን በዋና አዛዥነት የሚመራና የሚያሰማራ..» እያሉ እየፈረጁ፥ በአንፃሩ ለሻዕብያ የድርድር ጥያቄ አቅራቢዎች ደግሞ እራሳቸው መሆናቸው ብዙዎችን ያስገረመ ሆኖዋል።
ሲጠቃለል፥ ኢህአዴግ ራሱ ላወጣውና ለሚመፃደቅበት « ሕገ መንግስትና አዋጅ» ተገዢ መሆን አልቻለም። ይባስ ብሎ ሁሉም አዛዥና ፈላጭ ቆራጭ ሆኖዋል። የአቶ ሃ/ማሪያም ስልጣንና ሚና ውሉ አልለየም። የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ዋና አዛዥ ከአገሪቱ ቁልፍ ስልጣኖች ዋናው ነው። ማን ጋር ነው? የሚለውን ጥያቄ ከላይ ለማመላከት ተሞክሮዋል። ጥያቄው ግን አሁንም መነሳቱ ይቀጥላል። ጠ/ሚ/ሩ አውቀው ተኝተዋል። ይህ ስልጣን በየፊናው የሚያዝበት ስለበዛ..ወዴት ሊወስድ ይችላል?..የሚለው ለመገመት አያዳግትም። እየታየ ያለውም ይህንኑ ግምት የሚያጠናክር ነው!!
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
December 9, 2012

Thursday, December 20, 2012

“ከፓትርያርክ ምርጫ - ዕርቅና አንድነት ይቅደም” ስንል ምን ማለታችን ነው?

(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 12/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 21/2012/)፦ እንደሚታወቀው ቤተ ክርስቲያናችን በመስቀልያ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ተደጋግሞ የተገለጸ ነው ዋነኛዎቹ ርዕሰ ጉዳዮች ሁለት ናቸው። የመጀመሪያው ለ20 ዓመታት በውግዘት የተለያዩ አባቶች አንድ እንዲሆኑ፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን፣ አንድ አስተዳደር፣ አንድ ቅ/ሲኖዶስ እንዲኖረን ማድረግ ነው። ለዚህም “ተስፋ ሰጪ” ሁኔታ ላይ ተደርሷል። ይህ ዳር እንዲደርስ እናድርግ። ሁለተኛው ደግሞ 20 ዓመት ለቆየው መለያየት ዓምድና ምልክት የነበረው የፕትርክናው ሥልጣን አንዱ የመወያያ አጀንዳ ስለሆነ ከዕርቁ በፊት ሌላ እርምጃ አይደረግበት የሚለው ነው። ይህንን በሚጋፋ መልኩ በጥቂት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ግፊትና በመንግሥት ተጽዕኖ 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም “አስመራጭ ኮሚቴ” ተቋቁሟል። ሁለቱ አጀንዳዎች የሚገናኙት እዚህ ላይ ነው።

1.      ዕርቀ ሰላሙ ይፈጸም ማለት 4ኛው ፓትርያርክ የግድ ሥልጣኑን ይያዙ ማለት አይደለም። ሐሳቡ ውጪ በሚገኙት አባቶች በኩል የቀረበ መሆኑ ተደጋግሞ ተገልጿል። ለውይይት የቀረበ እንጂ ውሳኔ አይደለም። ውይይት የሚደረገው “ሰጥቶ በመቀበል ሕግ” አባቶች እንዲስማሙባቸው ሁሉንም አጀንዳዎች ጠረጴዛ ላይ ያስቀምጡ ማለት ነው።
2.     ምንም ቢሆን ከመለያየት አንድነት ይሻላል። ስለዚህ ዕርቁን ማስቀደሙ ተገቢ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን በመልዕክቱ አባቶቻችን ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ አንድነት የሚያመጣ ዕርቀ ሰላም መፈጸም ከሃይማኖታዊ ሥነ ምግባር አንጻር፣ ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ከማሰብ አንጻር፣ መንጋውን ከማነጽና ሐዋርያዊ አገልግሎትን ከማቅናት አንጻር ለአባቶቻችን ግዴታ ይሆንባቸዋል፡፡ የሚፈለገው ዕርቀ ሰላም እውን እንዲሆንም ለእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ለእውነት፣ ለኅሊና ምስክርነት መገዛት አግባብ ይሆናል” ሲል በትክክል ያስቀመጠውን ሐሳብ እዚህ ላይ ብንጠቅስ ተገቢ ይሆናል።
3.     አንዳንድ ሰዎች ስለ 4ኛው ፓትርያርክ ሲነሣባቸው የሚደነግጡበት ዐቢይ ምክንያት “የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ታሪክ ይደመሰሳል” ብለው በመስጋት ነው። እንደሚታወቀው ይህ ዕርቀ ሰላም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ የተጀመረ እንደመሆኑ ዕርቁ መሳካቱ ማንንም “የርሳቸው የቅርብ ሰው ነኝ” ባይ ሊያስደነግጠው አይገባም።
4.     ደጀ ሰላም ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን  በሚያደርጉት ተግባር ለረዥም ጊዜ ስትቃወማቸው እንደቆየች የአደባባይ ምሥጢር ነው። ስንቃወማቸው የነበረው ግን “በትክክል አልተሾሙም፣ ቀኖና የጣሱ ናቸው” ብለን አልነበረም። አይደለምም። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን 4ኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ከመንበራቸው ከተነሱ በኋላ “ባዶ መንበር አግኝተውና ተመርጠው” መሾማቸውን እናውቃለን። በወቅቱ ለተፈጸመው ጥፋት አቡነ ጳውሎስን ተጠያቂ ማድረግ ትክክል አይሆንም። በታሪክም በእግዚአብሔርም ፊት ሐሰተኛ ያስብላል። በመንግሥት ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት፣ በቤተ ክህነቱ ሰዎች ተባባሪነት 4ኛው ፓትርያርክ ሥልጣናቸውን ተቀምተዋል። አቡነ ጳውሎስ 5ኛ ፓትርያርክ በመሆናቸው አጠፉ ማለት ትክክል አይሆንም። ነገር ግን ቦታውን ከያዙ በኋላ በፈጸሙት ተግባር ግን (መሬት ይቅለላቸውና) ስንኮንናቸው ቆይተናል። አሁንም “እርሳቸውን እወዳለኹ” የሚል ቢኖር (በቤተ መንግሥቱ እንደሚባለው የርሳቸውን ራዕይ ለማስቀጠል) በእርሳቸው ዘመን የተጀመረውን ዕርቅ ማሳካት እንጂ ሌላ አማራጭ የለውም።
5.     የዘመነ አቡነ ጳውሎስ ግርግር ሳያንስ አሁን ደግሞ ሌላ የከፋ ልዩነትና ብጥብጥ እንዲፈጠር እየተደረገ ያለው ሩጫ በእጅጉ የሚኮነን ነው። ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ እንዳሉት “በፍፁም ተቀባይነት የለውም”። ብፁዓን አባቶች ከዚህ ታሪካዊ ስህተት ራሳቸውን ነጻ ማድረግ አለባቸው። እውነቱን ተናግረው መከራውን መቀበል ካልፈቀዱ ራሳቸውን ከዚህ ውሳኔ በማውጣት ከጥፋቱ ራሳቸውን ማዳን ይኖርባቸዋል። በዘመነ ደርግ ታላቁን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ለመከራ አሳልፎ ለመስጠት በተደረገው ስብሰባና ፊርማ ላይ የነበሩ አባቶች በሙሉ ዛሬ ስማቸውና ፊርማቸው ከነታሪካቸው ይፋ እንደሆነው ሁሉ አሁንም ቀን ሲያልፍ፣ ጊዜ ሲለወጥ በዚህ ድርጊት ውስጥ ያሉት አባቶች እያንዳንዳቸው አንገታቸውን የሚደፉበት ታሪክ እንዳይቆያቸው ቢያስቡበት መልካም ነው።
6.     ፓትርያርክ መሾሙ ያደርሳችኋል። መጀመሪያ አንድ ሁኑ።
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።
“እኔም የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል”
  
6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም የሚደረገውን ጊዜውን ያልጠበቀ ሩጫ አልደግፍም

Wednesday, May 16, 2012

ቅኝ የተገዛው ‹‹ የዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ›› እና የወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ባንዳነት ሲፈተሽ


ከጠቅላይ ቤተክህነት ከሚወጡት የሕትመት ውጤቶች አንዱ የሆነው ይህ ጋዜጣ መታተም ከጀመረበት ከ 1948 ዓ/ም እስከ 1967 ዓ/ም ድረስ ተወዳጅና ለብዙ አንባቢያን ተደራሽ ነበር፡፡ከ 1967 ዓ/ም በኃላ ጋዜጣው የሚያነሳቸው ሀሳቦች አወዛጋቢና ያዘጋጁን የተለጣፊነት ባህሪ አጉልተው የሚያሳዩ፣ ግለሰብን ማወደሻ፣ ቤተክርስቲን ማርከሻ መድረክ በመሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተነባቢነቱ ቀንሷል፡፡

Wednesday, May 9, 2012

አስኳሉ የተሐድሶ ሕዋስ ማኀበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡



እንቅስቃሴውን አቡነ ጳውሎስ፣ አቡነ ገሪማ፣ አባ ሰረቀ ብርሃን፣ በቅርቡ ከአሜሪካ ተመለሰው በአሜሪካ የኢትዮጵያ ///ያንና ጉዳይ ፈፃሚ የሆነው ኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን እና ሌሎች የቤተክህነት አጋሮቻቸው በህቡዕና በግልጽ ይዘውታል፡፡
ከውጭ ደግሞ መምህር ዘላለም ወንድሙ፣ቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ፣ መምህር ተስፋዬ መቆያ፣ቀሲስ አስተርአየ ጽጌና መምህር አቡኑ እያስተባበሩ ይገኛሉ፡

Monday, May 7, 2012

በሃይማኖተኝነት ሽፋን የነቀዙ ‹‹ሃይማኖተኖች››



ይህ ጽሁፍ ታደሰ ወርቁ የተባሉ ጸሐፊ በገጸ መጻሕፋቸው ያስነበቡን ሲሆን እኔም ቁም ነገሩን ስለወደድኩት ለተከበራችሁ የጡመራዬ ተከታታዮች እንድታነቡት እጋብዛለሁ፡፡


k²Ê ;|‰ xMST ›mT bðT bõb!à m{/@T NQzTN xSmLKè bqrb mÈ_F WS_ b¦Y¥ñt"nT >ÍN «¦Y¥ñt®C´ NQzTN XNÁT XNd¸f{Ñ yMTgL_ ¬¶K t-Qú xNBb@Ãlh#ÝÝ ¬¶k# XNÄ!H nWÝÝ b፲፱፻፶ãc$ mjm¶Ã §Y yyrR kr† xW‰© g¢E ynb„T Æl|LÈN ÂZÊT §Y yQDST ¥RÃMN b@t KRStEÃN bMXmn# mêô x\„ÝÝ bwQt$ k!n ?NÚW ytdnqWN b@t KRStEÃN ©NçY k¯bß# b“§ ðT lðT yt\‰WN DNQ mñ¶Ã b@TM tmlkt$ «YHN Ã\‰W ¥nW)´ BlW Y-Y”l#ÝÝ yxW‰©W g¢E MNM ;YnT mLS XNd¥Ys-# ytrÇT xrUêEW nUD‰S ts¥ X¹t& «©NçY¿ ¥RÃM \‰CW´ BlW xGDä> mLS s-# YƧLÝÝ

Thursday, May 3, 2012

የዋልድባ ገዳም አካባቢ የስኳር ልማት በአካባቢው ማህበረሰብ ቁጣ ቀሰቀሰ


ሙሉ ዘገባውን የወሰድነው ከአሜሪካን ድምጽ ድረ ገጽ ነው:: የአሜሪካን ድምጽ ዘገባ እንደሚከተለው ቀርቦዋል::

ለስኳር ልማት ሊውል ወደታቀደበት የዋልድባ ገዳም አካባቢ፤ ህዝብ ከተለያዩ አካባቢዎች እንዳቀና ምስክሮች ገለጹ።
ከተለያዩ የጎንደር ከተሞች የተውጣጡ በርካታ ነዋሪዎች፣ ዋልድባ ገዳም አካባቢ ይሠራል የተባለውን የስካር ፋፍሪካ በመቃወም፤ ወደ ግድቡ መሥሪያ ስፍራ እንደሄዱ ተሰምቷል።

በዚህም የተነሳ አንዳንድ ውዝግብ እንደተቀሰቀሰ ከአካባቢው ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየታቸውን የሰጡ ግለሰቦች ገልጸዋል።
በሃያም፣ በሃምሳም፣ በመቶም እየሆነ የተመመው ሕዝብ ማንም ያላሰባሰበውና ያላስተባበረው፣ ነገር ግን በራሱ ፈቃድ ጥሩምባ ነፍቶና ብሎ እንደሆነየአይን ምስርክር ገልጸዋል።

እንደምስክሩ አገላለጽ ጦር ያለው ጦሩን፣ መሣሪያ ያለው መሣሪያውን፣ ዶማና አካፋ ያለውም ያንኑ እየያዘ ነው ግድቡ ይሠራል ወደተባለበት ስፍራ የተጓዘው። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን፣ ወታደሮች ወደ ሕዝብ ለመተኮስ እንዳይሞክሩ መንግሥት ማስጠንቀቁንም እኒሁ ምንጭ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አንድ ከዚያው ከገዳሙ አካቢ ያሉ ቄስ «ከወልቃኢትም፣ ከጠገዴም፣ ከአድርቃይም፣ ከማይፀብሪም ባለሥልጣናት ተጠርተው ሥራው ሊቆም ተደራድረዋል፤ ለዚህም ቀጠሮ ለሚያዝያ ፳፱ ተይዟል» ሲሉ ለቪኦኤ ገልጸዋል።
በመንግሥት በኩል ላለው ምላሽ ከዚህ ቀደም አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ በመስጠት ወደተባበሩን፣ የማይፀብሪ አስተዳዳሪ ወደሆኑት ወደ አቶ ሲሳይ መረሣ ዘንድ ደውለን ለጊዜው ስብሰባ ላይ ስለነበሩ ማግኘት አልተቻለም