Thursday, March 1, 2012

ኢትዩጵያዊ ወኔ እና የዘመናችን ወጣት ማንነት


  
ከጣሊያን ወረራ 8 ዓመት ቀደም ብሎ የኢጣሊያ መንግሥት በቀይ ባሕር አካባቢ በ1870ዎቹ መጨረሻና 1880 መጀመሪያ (እኤዘአ) መስፋፋት ጀመረ፡፡በኅዳር 15ቀን 1869 ጂውሴፔ ሳፔቴ የተባለ መነኩሴ አሰብን አህመድ ሀሰን ቤን አህመድ ከተባሉ የአፋር ሱልጣን ገዛ፡፡
ሳቴፔ ይህን ውል የፈጸመው ሩባቲኖ በተባለ የኢጣሊያ የመርከብ ኩባንያ ስም ነበር፡፡በመጋቢት 1870 ጣሊያኖች የአሰብ ይዞታቸውን ማስፋፋት ጀመሩ፡፡በዚህ ሁኔታ በቀይ ባሕር ጠረፍ የመንደርደሪያ መናኸሪያ ለመትከል ቻሉ፡፡
በሰሜን በኩል የኤርትራ አገረ ገዥ በሆነው በአንቶኒዮ ባልዲሴራ ይቀነባበር የነበረው የቦርቦራ ፖሊሲ ሁለት ገጽታዎች ነበሩት፤ድንበር መግፋትና ትግራይ መሳፍንትን ማሸፈት፡፡ሆኖም ይህ የበርቦራ(የመለየት)ስራ ግቡን የመታ አልነበረም፡፡ይህ የበርቦራ ስራ እንዳልሰራላቸው ሲገነዘቡ ጣሊያኖች የቀራቸው አማራጭ ጦርነት ብቻ ነበር፡፡ ከዛሬ 116 ዓመት በፊት የአድዋ ጦርነት በወራሪው የጣሊያን መንግሥትና በአጼ ምኒልክ ጦር መካከል ሲደረግ የሞሶሎኒ ጦር የጦርነት ቅድመ ዝግጅት እና የመሳሪያ ክምችቱን ሲያጠናክር ቆይቶ፤ የተደራጀና የሰለጠነ ሰራዊት አስታጥቆ ኢትዩጵያን መሬት ወረረ፡፡አጼ ምኒልክ ከአምባላጌ ጦርነት  በ  ሁ ላ ጣሊያኖች   አዲግራትና ከእንጢቾ ምሽጋቸው ወጥተው ጦርነት የሚገጥሙበት ቀን በናፍቆት መጠባበቅ ጀመሩ፡፡ጦርነቱን በናፍቆት የሚጠብቅበት ምክንያት የሠራዊቱ ስንቅ ሁኔታ አሳሳቢ ስለነበር በስንቅ እጦት እንዳይበተን ስለሰጉ ነበር፡፡  ስለዚህም የኢጣሊያው ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጄኔራል ኦሬስቴ ባራቲዬሪ የካቲት 23 በማለዳ ድንገት አደጋ ለመጣል ጦሩን ማንቀሳቀሱ ሲታወቅ በኢትዩጵያ የጦር ካምፕ ከፍተኛ እፎይታ ተሰማ ፡፡ ባራቲዬሪ ይኸን እንቅስቃሴ ያደረገው ዕለቱ አንድም እሁድ ፤አንድም ደግሞ ዕለተ ጊዩርጊስ ስለሆነ ፤ኢትዩጵያውያን ድርብ በዓል ሲያከብሩ ድንገት አገኛቸዋለሁ በሚል ግምት ነበር፡፡በዚህ ግምት እንዲገፋበት ያደረጉትም ለምኒልክ መረጃ በማቀበል ፤ለጣሊያኖች ደግሞ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ፤ለአድዋ ድል አስተዋጽኦ ያደረጉት እንደ አውዓሎም  ያሉ ቆራጥ አርበኞች ናቸው፡፡

ዛሬ በሃገራችን ቅኝ አለመገዛት፤የራሳችንን ባህልና እምነት ጠብቀን መኖራችን፤በድፍረትና በወኔ እንድናወራና እንድንኮራ ያደረጉን ጀግኖች አባቶቻችን አፈሩ ይቅለላቸው ነፍሳቸውን ከደጋጎቹ ይደምርል፡፡ ግን ግን ዕድሜ ለዘመናችን መሪዎች ባርነትን አሜን ብለን እንድንቀበል፤ሃገራዊ ስሜት ሳይሆን የጎጥ መዝሙር እንድንዘምር ቦታና ጊዜ እየቀያየሩ ያሰለጥኑናል፡፡ሁሉም ከትውልድ መንደሩ (የዘር ሃረጉ ) ውጭ ለማሰብ የተፈጠረ ሕሊና መኖሩን ዘንግቶ እኔ ኦሮሞ፤ ትግሬ፤ ሐረሬ፤ሱማሌ፤ አማራ ፤ ደቡብ ፤ቤኒንሻንጉል----------- ምን የማይለው አለ?
አሁንማ ጭራሽ ‹‹ዘፋኝ››ተብዬዎቹ ሃገር ማለት ትርጉሙ ጠፍቶባቸው  ሃራምባና ቆቦ ሲረግጡ አብረን እናንቃርራለን የራሳቸውን በሽታ በባዶ ጩኽት ሲያቀብሉን ሳናኝክ እንውጣለን፡፡ከጫትና ሲጋራ የራቀ ህልም የሌላቸው ባዶ ጋኖች ሆነው ሳለ እነሱን ካልመሰልን ደስ አይለንም አለመታደላችን፡፡መንግስትስ ቢሆን ሜዳውን በእሾህ አለስልሶ የስልጣኑ ማራዘሚያ እና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲዉን ለ20 ዓመታት ሲያካሂድ ባለህሊና ሰዎች በውስጡ ጠፍተው በእንድ ጋን እንደተዘጋጀ ሆምጣጤ ንግግራቸው፤ ፖሊሲያቸው፤ ወዘተ በሙሉ ሃገሪቱን የምትመራው በባእድ እንጂ በእናት ሃገር ልጆች አይመስልም፡፡ያኔ አያቶቻችን ህዝቡን አስተባብረው ጠላትን ድል እንዳላደረጉ፤ የቀደመ ክብራቸውን ለማጉደፍና ድሉን የአንድ ብሔር ብቻ እንደሆነ በአዲስ አጀንዳ አየሩን በመበከል ተጠምደዋል፡፡
ይቀጥላል፡፡
ኢትዩጵያ ለዘለዓለም ትኑር፡፡

No comments: