Saturday, April 28, 2012

ደጀ ሰላም Deje Selam: ዋልድባ አሁንም አወዛጋቢነቱ እንደቀጠለ ነው (ጥልቅ ሪፖርታዥ)

ደጀ ሰላም Deje Selam: ዋልድባ አሁንም አወዛጋቢነቱ እንደቀጠለ ነው (ጥልቅ ሪፖርታዥ): READ THIS ARTICLE IN PDF . ·          ማኅበረ ቅዱሳን በዋልድባ ጉዳይ ከፓትርያሪኩ እና ከመንግሥት ጋራ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።  ·     ማኅበሩ የወልቃይት ስኳር ፕሮጀክት በዋልድባ ገዳም...

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: በእንግሊዞች የተመራው የመቅደላው ዝርፊያ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: በእንግሊዞች የተመራው የመቅደላው ዝርፊያ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ:   click here for pdf በፍቅር ለይኩን፡፡ [ fikirbefikir@gmail.com] «በጣም ከሚያስገርመውና ከሚያሳዝነው ነገር ሁሉ በመቅደላ በንጉሡ በአፄ ቴዎድሮስ ታስረው ከነበሩት እንግሊዛ...

Tuesday, April 24, 2012

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: ፍቅር እና ሀገር

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: ፍቅር እና ሀገር: click here for pdf ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢየሩሳሌምን ለመጀመርያ ጊዜ ለማየት መጥቼ ነበር፡፡ ስመለስ አውሮፕላኑን የሞሉት ቤተ እሥራላውያን ነበሩ፡፡ በመካከሉ አንዱን ሽማግሌ ...

Sunday, April 22, 2012

አደባባይ: “ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም”

አደባባይ: “ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም”: ( READ IN PDF ):- ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ እንደተለመደው የምክር ቤቱ ክቡራን አባላት በንባብ ላቀረቡላቸው ጥያቄዎቻቸው ...

Saturday, April 7, 2012

144ኛ ዓመት የአፄ ቴዎድሮስ ዜና ዕረፍት ሲታሰብ



ማረክን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው
ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኙአቸው
ምን አሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው
ለወሬ አይመቹም ተንኮለኛ ናቸው፡፡
ከጣና ሐይቅ በስተሰሜን ምዕራብ በምትገኘው የቋራ ወረዳ ውስጥ ሻርጌ ከተባለው መንደር በ1811 ዓ.ም. ተወለዱ ካሣ ኀይሉ /ካሣ ማሩ/ይሏቸዋል፡፡
የካሣ ኀይሉ አባት ሐይለ ማርያም ቋራ ውስጥ መስፍን ነበሩ፡፡ ደጃች ማሩ የማኅበረ ሥላሴን ገዳም የአብነት ተማሪዎችን በተለይ የያኔው የመኳንንት አጎታቸው ደጆች ክንፈ በትምህርት እንዲያድጉ ካሣን ወደ ማኅበረ ሥላሴ ገዳም ወስደቸው በገዳሙም ዳዊት ጨርሰው ሌላ ትምህርት ለበሚማሩበት ጊዜ ልጆቹ ወላጆቹን ለመበቀል ፈለጎ ወጣቶቹን የመኳንንት ልጆች በጥይት ፈጃቸው /አንዳንድ ድርሳናት ደግሞ ለጆቹን ሰለባቸው/ ይለዋል፡፡ ካሰም ከእላቂቱ አምልጦ በእግሩ ወደ ትውልድ አገሩ ተሰደደ፡፡ ከዚህ በኋላም ክንዳቸውን በመተማመን ከሚኖሩ ሽፍቶች ጋር ተቀላቀለ፡፡ ይህ ሽፍትነት ከባዱን የወታደራዊ ጥበብ /ትምህርት/ አስተማረው፡፡ ለለጆች ጎሹ የጎጃም ባላባት በማደር አገር ማስተዳደር ሲባል የለውጥ ጣጣ በማወቅ ዕድል አገኘ፡፡ በመቀጠልም የደጃች ጉሹ ወታደራዊ አማካሪ ሆነ፡፡

የተለያዩ የጦርነት አውደ ውጊያዎች በድል የተወጡት ካሣ ኀይሉ የካቲት 5 ቀን 18 47 ዓ.ም. ደረሰጌ ማርያም ላይ በፓትርያርኩ በአቡነ ሰላማ አማካኝነት የኢትዮትያ ንጉሠ ነገሥት ተብሎ ዘውድ ጫነ የሰላሳ ሰባት ዓመት ጎልማሳ የነበረው ካሣ ኀይሉ ዳግማዊ ቴዎድሮስ የሚለውን የዙፋን ስም መረጠ፡፡
በኢትዮጵያ የአንድነት ታሪክ ከፊት ከተቀመጡት መሪዎች ውጥ ቀዳሚው አፄ ቴዎድሮስ ናቸው፡፡ በመሳፍንታዊ አገዛዝ ሥር እንደ ቅርጫ ሥጋ በመደብ ተከፋፍላ የነበረችው ወደ አንድነት ለማምጣት ራዕይ ሰንቀው የተንቀሳቀሱ መሪ ነበሩ፡፡ ሸዋንም …. ካረጉ በኋላ ታላላቆቹን የኢትዮጵያ ቀበሌዎች አንድ አድርገው በሥልጣናቸው ሥር አዋሉ፡፡ 17 ጊዜ የግድያ ሙከራ የተደረገበት አፄ ቴዎድሮስ መላ ሀገሪቱን በመሣሪያ ኀይል ገርቶ ማንኛውንም የመገንጠል አዝማሚያ ገና በጅምሩ እየቀጨ ሲቆጣጠር የመጣ ንጉሠ ነገሥት የማያንቀላፋውን የባላባቲዊ ኀይሎች አውድ አደጋ ላይ የጣለውን የመንግሥቱን ፖለቲካዊ አንድነት ለመጠበቅ ሞክሯል፡፡
የዳግማዊ ቴዎድሮስ የውጭ ፖሊሲ
ቱርኮች በ16ኛው መ.ክ.ዘ. ጀምሮ በቀይ ባሕር ላይ አንዳንድ ጊዜ እየተቋረጠ ከሦስት መቶ ዓመት በላይ የምጽዋን ወደብና የዳህላክን ደሴቶች የጦር ሰፈር አድርገው ኢትዮጵያ ከሌሎች አገሮች ጋር ግንኙነቷን እንድታደርግ አፍላዎች ኑረዋል፡፡ በ1860 አካባቢ ደግሞ የምጽዋን ወደብ ለዘለቄታው lለግብጽ አስተላለፈ፡፡ የታጁራን ሰርጥ አካባቢ፣ ዘይላና በርበራ ያዙ ይህ የግብጽ መስፋፋት በዳግማዊ ቴዎድሮስ በኩል ቆራጥ ተቃውሞ ገጠመው የሀገር ውስጥ አቋሙን ካጠናከረ በኋላ በውጭ ፖሊሲ ረገድ ታላላቅ እቅዶችን ነደፈ፡፡ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሰጠውን ግብጻውያንን ጠራርጎ በማስወጣት ኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤት የማድረጉን ተግባር ነበር፡፡ ይህም ዐሳቡ ሰሜን ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የውጭ ፖሊሲ ውስጥ እጅግ የጎላ ስፍራ ያለው ጉዳይ መሆኑን ከተገነዘቡ ታላላቅ ተደናቂ የኢትዮጵያ መሪዎች አንዲ ያደረገው ዳግማዊ ቴዎድሮስ ከአረቦች ጋር በሚደረገው ትግል ውስጥ ታላቅ ብራታንያ ጋር ግንኙነት ማድረግ ጀመረ፡፡ ፕላውደን የተሰኘ እንግሊዛዊም በይፋ በኢትዮጵያ ብሪታንያ ቆንስላ ሆኖ ሥራን ማከናወን ያዘ፡፡ፕላውደን ስለታመመ ከጆን ቤል ጋር በጎንደር በኩል ጉዞ እያደረጉ እያሉ ጋራጅ በዳግማዊ ቴዎድሮስ ላይ አምደ ስለነበር በመንገድ ላይ አደጋ ጣለባቸው በነሱም በድኑ ቆስሎ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሞተ፡፡ በኋላም በጋራድ ላይ ሌት ተቀን ክትትል ተደርጎ እሱና ግብረ አበሮቹ ተከበው ተጨፈጨፉ፡፡
ከእንግሊዝ ጋር ውዝግብ
በየካቲት1862 አዲሱ የእንግሊዝ ቆንስል ሻምበል ካሜሮን ወደ ኢትዮጵያ መጣ፡፡ ካሜሮን አፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዝ መሐንዲሶች በተለይም የጦር መሣሪያ ስፔሻሊስቶችና ሐኪሞች እንዲመጡለት እንደሚፈልግ ለብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ቢሆንም ሎርድ ረስል አፄው ያቀረበው ዐሳብ ጨርሶ አልወደደውም ይባስ ብሎም ሻምበል ከሜሮን ኢትዮጵያን ሰቆቃ እንደወጣ እና ወደ ምፅዋ እንዲሔድ ካዘዘው፡፡ የእንግሊዝን አቋም የተረዳው አፄ ቴዎድሮስም ካሜሮን አስረው፡፡ ስዕሎችም 40 የሚሆኑ አውሮፓውያን ያዙ፡፡

የዳግማዊ ቴዎድሮስ ውድቀትና ሞት
ካሜሮን ከታሰረ በኋላ የእንግሊዝ መንግሥት በድርድር ሊያስፈታው ሙከራ አድርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን የታሰሩት አውሮፓውን የሚለቀቁት እንግልር ጦር መሣሪያ የማምረት ትሎታ ያላቸው ሠራተኞች ስትልክና የመሥሪያ ፋብሪካም ለማቷቷም የምትረዳ ከሆነ ነው ሲል፣ ለራሱም አስረዳው ከእንግሊዝ መንሥስት በኩል ምላሽ እስኪመጣ ራሳምን በኢትዮጵያ እንዲቆይ አድርጎታል፡፡
“የታሠሩ አውሮፓውያን ለማስፈታት” በሚል ህንደዊው በጄነራል ናፒየር መሪነት የወታደራዊ ኀይል አዘመተች ጥር 3 ቀን 1860 ዓ.ም.15.000 የብሪታንያ ጦር ጠቅልሎ ኢትዮጵያ ገባ፡፡ ሠራዊቱ 9000 ድጋፍ ሰጭ ኀይል ታክሎበት በጠቅላላው 26.000 ነበር፡፡ አንዳንድ ምንጨች 32.000 ያደርሱታል በኋላም በ1860 በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው የብሪታንያ ጦር ኀይል 45.000 ሰው ደርሷል፡፡ ይህ ዘመቻ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ ወጭ ወጥቶበታል፡፡
እንግሊዞች ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው ወደ መቅደላ በሚያደርጉት ጉዞ አንዳችም ተቃውሞ አልገጠማቸውም፡፡ የላስታው ዋግሹም ጎበዜና የትግሬው በዝብዝ ካሣ /አፄ ዮሐንስ/ ከእንግሊዞች ጋር ተጎዳኙ፡፡ እንግሊዞች በአካባቢው ካሉት አጋሮቻቸው ቴዎድሮስ ስላዘጋጀው ወጥመድ በቅድሚያ አውቀው ስለነበር ድንገተኛ ጉዳት ሳይደርስባቸው ቀርቷል፡፡ በርካታ በማሳለፍ ፈንታ ጦርነቱን በመድፍ ብቻና 2.000 ወታደር አሮጌ በተባለ ቦታ ሊያሸንፈው ችሏል፡፡
ቀደም ሲል እንዳየነው ንጉሠ ነገሥቱ ታላቅና አንድነቷ የጸና ኢትዮጵያን የማምጣት ዕቅድ ገና የእንግሊዝ ጦር ከመምጣቱ በፊት በሀገር ውስጥ ባሉ ከፋይሉ ኀየሎች አማካኝነት ተበላሽቶ ነበር፡፡
ሚያዚያ6 ቀን 1860 ዓ.ም. አፄ ቴዎድሮስ ለእንግሊዝ እጄን አልሰጥም በማለት በገዛ በተወለዱ በ50ኛ በነገሡ በ14ኛው ዓመት ሽጉጣቸው ራሳቸውን አጠፋ፡፡ በመቅደላ መድኅኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ፡፡
የንብረት ምዝበራ/ ዘረፋ
ከዚህ በኋላ በተከተለው ቀውስና ውጥንቅጥ እጅግ መጠነ ሰፊ የሆነ የንብረት ዘረፋ ተካሔደ በዚህ አጋጣሚ የቴዎድሮስ የወርቅ ዋንጫ፣ የንጉሣዊ ዘውዱ እና የፓትሪያሪኩ ዘውድ ተወሰደ፡፡
በሺዎች የሚቆጠር የሀገሪቱ ጥንታዊ ድርሳናትና መጻሕፍት፣ በእጅ የተጻፉ ቅዱሳን መጻሕፍትና ክብረ ነገሥት፣ አሥር ታቦቶችን፣ የተለያዩ ንዋየ ቅድሳትን የወርቅ፣ የብረት፣ የነሐስ መስቀሎችን አያሌ የብራና ጽሑፎችንና የአቡነ ቆብና ታላቁ ማኅተመ ሳይቀር ተመዘበሩ፡፡
በ15ዝሆኖችና በ200 በቅሎዎች ጭነው ወደ ደላንታ አምባ ወሰዱ፡፡ በዘራፊዎች የማይፈለጉት ድርሳናትና የጥበብ እጅ ሥራዎች ተወረወሩ፡፡ ንብረቶቹም በአምባው ላይ በ5 ኪሎ ሜትር ያህል ተበትነው ተዝረክርከው ይታዩ ነበር የተዘረፈው ንብረት በሁለት ቀናት ለጨረታ ቀርቦ የነበረ ሲሆን ዘመቻውን ተቀላቅሎ የመጣው የብሪታኒያ ሙዚየም ባልደረባ ዋና ተጫራች ሆኖ ነበር፡፡
የእጅ ጥበብ ሥራዎቹ በዛሬ ወጋ አንድ ነጥብ አራት ቢሊዩን /1.5 ቢሊዮን/ የኢትዮጵያ ብር ያህል ይሆናል፡፡
በተለያዩ ጊዜያት በዚሁ ወቅት ተዘርፈው ከሀገር የወጡ ቅርሶች ከሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ብርቱ ጥረትና የዲፕሎማሲያዊ ግፊት ወደ ሀገር ቤት እየተመለሱ ይገኛሉ ከዚሁ የአፄው ልደት ጋር አብሮ የሚዘከረው ወደ ሀገር ቤት የተመለሰው የመቅደላ መድኀኔዓለም ጽላት ግንቦት 28/2004 ዓ.ም ወደ መንበሩ ይመለሳል ፡፡

Wednesday, April 4, 2012

አደራ


መፅሃፍ አንብቤ ፤እፎይ ባልኩ ሰዓት

ምነው ዛፍ በሆንኩኝ፤እያልኩ እመኛለሁ


 
ወይ ፍሬ አፈራለሁ
ወይ ጥላ እሆናለሁ
      ቢያንስ አንዲት ወፍ በግል
                               አምና ጎጆ ቤቷን ፤እንደምትሰጠኝ እተማመናለሁ
             ያኔ በትክክል ለአደራ እበቃለሁ፡፡
(ስውር ስፌት ከተሰኘው የነቢይ መኮንን የግጥም መጽሐፍ የተወሰደ 1999ዓ›ም)