Wednesday, February 15, 2012

‹የምርጦች ምርጥ አዋጅ››የሽብርተኝነት አዋጅ

 
ከትናንት ወዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የሃገሪቱን የስድስት ወር ሪፖርት አቅርበው ነበር፡፡እኔም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግሮች የታዘብኩትን ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡
ዘወትር ፌዝ የማይለው የሃገራች ምክር ቤት ዛሬም የህዝቡን ብሶትና ሮሮ እንደመስማት የተጻፈላቸውን እና የታዘዙትን እንዲጠይቁ በማድረግ በትውልድ ላይ ዛሬም መቀለዳቸውን ቀጥለዋል፡፡ኢትዮጵያየ ለዚህ በቃሽ ?‹‹ሃገር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል፡፡››ይሉ ነበር አባቶቻችን፡፡ይኸው ዛሬ በእኛ ዕድሜ አየነው የመከራ ገፈት ቀማሽ ፤የችግር ተቐዳሽ ሆንን፡፡ይባስ ብሎም ግብር ከፍለን ባቆምነው ሚዲያ ሃያ ኣመታች እየተሰድብን አለን፡፡ድሮም በእብሪት የተሞላ ሕሊና ከሆዱ ባለፈ ለሃገርና ለወገን የማሰብ እንጥፍጣፊ መልካም እሳቤ ያልፈጠረበት የዘመናችን ጉድ i
ጆሮ አይሰማው የለ የሽብርተኝነት አዋጁ ከብዙ ሀገራት የተቀዳ /የተኮረጀ/ የምርጦች ምርጥ አዋጅ ነው ሲሉ ያንቆለጳጵሱታል፡፡እኔ ምለው ግን ይች ሃገር ከውጭ የሚገባ እንጂ እዚሁ እኛ ሃገር የሚሰራበት በጎ ተሞክሮ የለም ማለት ነው ? የነጮቹ ህግ ብቻ ነው የእኛን ሃገር ፖለቲካ መፍትሄ የሚሰጠው እንዴ? ለነገሩ ምን ታደርግ ፤ከማንስ ትማር አባትህ ያወረሱህ ነው ይዘህ ያደግከው፡፡ድሮም የባንዳ ልጅ ባንዳ ነው፡፡ዘር ከምን ይስባል አይደል ትረቱስ፡፡
ምነው ታዲያ አፋኝ አፋኙን ብቻ መምረጥዎ? ነጮቹ እኮ ብዙ የብዙ ብዙ ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ምህዳር አላቸው እንደኮራጅ እሱንም አብሮ መሞጭለፍ ነበር እንጂ አንዱን ያዝ ሌላውን ለቀቅ ቂልነት ነው፡፡በሌላው የኩረጃ ስምሪት ጊዜ ግን አደራ አደራ እንዳይረሳ ፡፡ሌላው ጥሩ አማራጭ ደግሞ ቻይና ያሉት ልጆቻችሁን ነጻ የምርጫ ስነ-ምህዳር፤ነጻ ሚዲያ ሽፋን ፤የመሰብሰብ፤ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፤የሰብአዊ መብቶችን የማክበር--------ዘዴን ባሉበት political boarding school የስነ ምግባር መመሪያ ሆኖ ቢሰጣቸው ወደ አባት ሃገራቸው ሲመለሱ ግር እንዳይላቸው ስለሚያደርጋቸው ቢታሰብበት መልካም ነው፡፡በተለይ ጨዋው የኢትዮጵያ ህዝብ ‹‹ሺህ ዓመት ይንገሱ››ብሎ እጅ ሲነሳ (ጣት ሲቆርጥ አላልኩም) እነሱም ለክብሩ የሚመጥን ዉዳሴ ህዝብ እንደሚያቀርቡ አምናለሁ፡፡
የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትራችን እባክዎትን አሁንም ምርጥ ምርጥ ተሞክሮዎችን ወደ ሃገር ቤት Import በማድረግ የአባትዎትን ሃገር በባዕዳን ተሞክሮ ወደፊት ያራምዱ------------፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር፡፡

No comments: