Wednesday, February 15, 2012

ኑሮ እና ሮሮ

 
ዕለቱ ቅዳሜ ነው፡፡ካሳለፍት ጊዜያት በተለየ ራሴን እንድፈትሽ አጋጣሚ የፈጠረ ዕለት፡፡በህሊና ከራሳችሁ ጋር ተማከሩ የለ ? እኔም ከዘወትሩ በተለየ ሁኔታጥልቅ ሃሳብ ገበቶኛል፡፡የወገኔ ኑሮ እና ሮሮ፡፡
በታከሲ ውስጥ ፤በየመስሪያ ቤቱ፤በየዩኒቨርሲቲው ግድግዳና መጸዳጃ ቤት የሚጻፉት ወጎች ቀልቤን ስበውታል፡፡ደርሶ ዛሬ ለምን በተለየ መልኩ ትኩረት እንደሰጠሁት አልገባኝም፡፡ለወትሮው ለዘብተኛ (ሊበራል) ከሚባሉት ወገን ነህ ይለኝ ነበር ባልንጀሮቼ፡፡ምንም አይገድህም …..ሀገር ብትለማም ብትጠፋም አንተ ሁድህ ከሞላ የሌላው ማጀት ትዝ አይልህም ሲሉ አሽሙር መናገራቸው ነው በእነሱ ቤት iii
እስኪማን ይሙት…….. ? አሁን በሀገራችን ምን ጠፍቶ ነው ? ርሃብ፤ የኑሮ ውድነት ……ወዘተ የሚባለው ?
በዚያ ሰሞን የተከበሩ ጠቅላይ ሚስትራችን ያሉትን አልሰማችሁም ማለት ነው እንዴ ? በሞቴ ላፍታ ላስታውሳችህ ‹‹በሃገራችን ችጋር እንጂ ርሃብ የለም››አይደለም ያሉት ? ታዲያ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ ከየት ሊመጣ ነው ወዳጆቼ ?
በተከታታይ አምስት ዓመታት 11.5 በመቶ እድገት አሳይተናል፡፡ይህ ፈጣን እድገታችን አንዳንድ ጸረ -ልማት ሃይሎች ለማደናቀፍ ቢሞክሩም በህብረተሰቡ ትብብርና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ክትትልና ርብርብ እድገታችንን በፈጣን ሁኔታ ማስቀጠል ችለናል፡፡ ደግሞስ በየመጠጥ ቤቱ እና ስጋ ቤቱ የሚቀርበውን የመጠጥ እና የቁርጥ አይነት ‹‹ያያና ተመገበ››ይፍረደኝ፡፡የኢኮኖሚያችንን እድገት ፖል ቴርጋት እንኮዋ አድቫንስ ሰጥተነው አይደርስብንም፡፡ታዲያ አንዳንድ አይናቸውና ጆሮአቸው ክፉ ክፉው ብቻ የሚስመለክታቸውና የሚያሰማቸው ርሃብ፤ የኑሮ ውድነት ፤የስራ እጦት ቅብጥርሴ ያስለፈልፋቸዋል ፡፡ ይህ የቅናት ዛር ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል? አንድ ኪሎ ስጋ 110 ብር እኮ እኛ ሃገር ነው አዎ የሚሸጠው በሞቴ ውጭ ያለ ወዳጅ ወይም ዘመድ ካለ በዚህ ብር ምን ሊገዛበት እንደሚችል ጠይቁት እና መልሱን ጻፉልኝ፡፡በእግጠኝነት አንድ በርገር እንç የመግዛት አቅም እንደለለው አስረግጦ እንደሚነግራችሁ ተስፋ አለኝ ፋሽስታዊ ስርዓት ካልሆነ በቀር፡፡
ደግሞ 2.4 ትሪሊዮን ብር ከሃገር ሸሸ እያሉ የሚያወሩ አሉ አሉ ? የምእራባውያን ሚዲያ እኮ ሃገሪቱ ብትፈርስ ደስታቸው ነው፡፡ቀን ከሌት እየሰሩበት ያለውም ርዕሰ ጉዳይ ኢትዮጽያና ኢትዮጽያዊነት ላይ ብቻ ሆኖአል፡፡አንዳንድ ጊዜም ከእኛዎቹ ሚዲያዎች በይዘትም በጥራትም ይበልጣሉ ሲሉ የሚከራከሩ ቢኖሩም እኛ ለወጣቶቻችን የምናስብላቸውን ቅንጣት ለጫትና ለሲጋራ የማይሸፍን ተቅዋም ይዞ መንቀሳቀስ የትም አያደርስም እኛ እኮ በዘፈን(ሙዚቃ ) ፤ሀሽሽና ጫት በገፍ ከየቦታው በማስመጣት አደገኛ ቦዘኔ እንዳሆንብን አጥብቀን እንሰራለን፡፡‹‹ለተቀናጀ የማደንዘዝ አጀንዳ እንሰራለን››አይደል ‹‹እኛ ሚዲያዎችስ›› የሚሉት፡፡
እናም ወገኔ ፈረንጆቹ በወረፋ ምግብ መታደል ሲጀምሩ እኛ ደግሞ በምግብ ራሳችንን ስንችልና በቀን ሶስት ጊዜ በልቶ የሚያድር አርሶ አደርና አርብቶ አደር ባፈራንበት በዚህ ወቅት ሃገራችንን በሲኦል ደጅ ባትመስሉብን ጥሩ ነው፤ቢያንስ ቢያንስ ለገጽታችን፡፡አንዳንድ ጀግና የልማት ሰራዊት አባላት ቤታቸውን በቆርቆሮ ፤ አጥራቸውን በግንብ፤ኑሮአቸውን(በርሃብ አላልኩም እንዳትሳሳቱ) በምቾት ባደረጉበት በዚህ ወቅት አመድ ለመነስነስ የሚደረገው ሩጫ ለማንም የሚበጅ አይደለም፡፡በመሆኑም የእኔን ምክር ስሙኝ እባካችሁ እረፉና ርሃባችሁን አስታሙ፡፡ያለን ይበቃናል!!! ሌላ ርሃብ፤ ችጋር……..እንዳይመጣብን ስለኑሮ ሮሮ አታሰሙን ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡

No comments: