Wednesday, April 4, 2012

አደራ


መፅሃፍ አንብቤ ፤እፎይ ባልኩ ሰዓት

ምነው ዛፍ በሆንኩኝ፤እያልኩ እመኛለሁ


 
ወይ ፍሬ አፈራለሁ
ወይ ጥላ እሆናለሁ
      ቢያንስ አንዲት ወፍ በግል
                               አምና ጎጆ ቤቷን ፤እንደምትሰጠኝ እተማመናለሁ
             ያኔ በትክክል ለአደራ እበቃለሁ፡፡
(ስውር ስፌት ከተሰኘው የነቢይ መኮንን የግጥም መጽሐፍ የተወሰደ 1999ዓ›ም)
 

No comments: