Wednesday, March 7, 2012

ወጣት የነብር ጣት

ባለፈው ጽሁፌ ስለጣሊያኖች በአሰብና በቀይ ባህር አካባቢ ያደረጉትን መስፋፋት ፤በኋላም የጦርነት ሂደቱን በአጭሩ ጠቅሼ የኢትዮጵያን ታሪክ አንሸዋረው እያዩና እየተናገሩ ያሉትን የወያኔ አፈ ጮሌዎች  እና የዘመናችንን ወጣት ሁኔታ በአጭሩ ዳስሻለሁ፡፡ዛሬም ወጌን ልቀጥልና እንጨዋወት፡፡


መንታ መንገድ ናቸው መጥፋትና መዳን፤

ምንም መሪ የለን ፤፤ለዚህ የሚረዳን፤

ብርሃን የሚሰጡን ፤ጮራ ሁነው መብራት፤

ሁለት ስልቶች ናቸው፤ ድፍረትና ፍርሃት፤

ድፍረት ወንድነት ነው፤ለሰው የሚስማማ፤

ፍራት በሽታ ነው፤የሞኝ የደካማ፤

ለኔ የሚሆነኝ ከእነዚህ ሁለቱ፤

ማንኛው እንደሆን፤ በውተኛው የቱ፤

አልቻልኩም ለማወቅ ፤አልመረጥኩም ገና

እውላለሁ ጉዳዩን ሳጠና፤

ሆኖም ተሰምቶኛል ፤የሕይወቴ ዕጣ
የምወስንበት እንደመጣ፡፡

       (ከከበደ ሚካኤል የቅኔ ውበት የተወሰደ)
በሕብረ ብሄራዊ ስሜት ከአውሳ እስከ ጅጅጋ፤ ከሐረር አስከ በጌምድር ፤ከጅማ እስከ ትግራይ ፤ከወላይታ እስከ ወሎ ያሉት አውራ የጦር አበጋዞች፤እንደራሴዎች ፤አኩራፊ ሽፍታዎችና የውስጥ ባንዳዎች ሳይቀሩ ጦርነቱ ቁርጥ መሆኑን ሲያውቁ፤እምቢ ላገሬ ብለው በአንድ ድምጽ ጠላት በአንድነት በመውጋት  አድዋ ባለታሪኮች ሆነው አልፈዋል፡፡ይህ ሃገራዊ ድል ስሜት እየቀዘቀዘ ሲመጣ ይመስላል ኢትዩጵያ እንዲህ ስትል ትወቅሳለች፤የዘመናችንን ወጣት፡-


ተነሡ ተነሡ እናንተ የተኛችሁ፤

እስከ ዛሬ ድረስ ወዴት ነበራችሁ፤

ምንስ እስኪሆን ነው አሁን ዝምታችሁ፤

በቅጡ እንዲጠበቅ ዙሪያው አገራችሁ፤

እንቅስቃሴ አርጉ በየከተማችሁ፤

በቶሎ ተፋጥነው ይሥሩ እጆቻችሁ፤

እንዲያገለግለኝ ለኔ ለናታችሁ፤

ሳትከፋፈሉ ባንድነት ሆናችሁ፤

ነውራችሁን ፋቁት ሳይጠፋ ስማችሁ፡፡
ይህ ግጥም ግንቦት 14 ቀን 1918 ዓ.ም በቲያትር መልክ አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን ኃይለ ሥላሴ  ባሉበት መድረክ ቀርቦ የነበረ ሞጋች ግጥም ነው፡፡
ወጣት የነብር ጣት
ትንታጉ ወጣት የጨረተ አስተሳሰብ ማራገፊያ አይሆንም ሆኖም አያውቅም፤ሃገራዊ አንድነት ለማፍረስ (በመንደርና በጎሳ ፖለቲካ) ሌ
ከ ቀን እየተጋ ያለውን ወያኔ ተው ፤በቃህ የምንልበት ወቅቱ አሁን ነው፡፡የዘመኑ ወጣት ያለፈውን ታሪካችንን እንደ ወርቅ አንጥሮ መልካሙን ሲይዝ ዘመን አመጣሹን የምእራብ አስተሳሰብና ተሞክሮ ሃገሩን ለማልማትና ወደቀደመ ክብርዋ ለመመለስ ይጠቀምበታል እንጂ የወንበዴ ዕድሜ ማራዘሚያ አይሆንም ፡፡
 ኢትዩጵያ ለዘለዓለም ትኑር፡፡

No comments: